Featured

First blog post

This is the post excerpt.

Advertisements

This is your very first post. Click the Edit link to modify or delete it, or start a new post. If you like, use this post to tell readers why you started this blog and what you plan to do with it.

post

የአማራ መደራጀት ጥያቄዎች

ከማተቤ መለሰ ተሰማ
በአለፉት ሁለት ሳምንታት በአማራው መደራጀት ዙሪያ በአስነበብኋቸው ሁለት ተከታታይ መጣጥፎች መነሻነት። በኢሜል አድራሻየ ከቅረቡልኝ በርካታ ጥያቄዎች መካከል። «አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይነቃም እንዲሉ» ጽሁፌን አውቀው በተንሸዋረረ አይን የተመለከቱትን ትቸ። ቅን ከሆኑ ኢትዮጵያዊ ተደራስያን ከመጣልኝ በዛ ያለውን የሚሸፍነው። ህብረ ብሄር ድርጅቶች የሚያደርጉት ሁሉን አቀፍ ቅንቅስቃሴ ስላለ። አማራውን እንደ አዲስ ከማደራጅት ይልቅ እነሱን በማጠናከር ወያኔን ማስወገዱ ተመራጭ አይሆንም ወይ። ትግሉ ተጠናክሮ ህዋሃት መራሹ ስርአት ተወግዶ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ችግር ሲፈታ የአማራውም ችግር አብሮ ይፈታል የሚለው የጎላ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።
ነገሩ እውነት ነው ሌሎች በዘራቸው ተደራጅተው አማራውን ማጥቃቱን ባይቀጥሉበት ኖሮ ከዚህ የተሻለ አማራጭም አቋራጭም መንገድ አይኖርም ነበር። አማራውም እንደዚህ እያሰበ ነበር 26 አመት ሙሉ በሁሉም ወገኑ በሁሉም አካባቢ ሰይፍ ተመዞበት ሲገደል፣ ሲሳደድና ሲዋረድ ዝም ብሎ እየወረደበት ያለውን መአት ሲቀበል የኖረው። አሁን ግን እጅግ በጣም በዛ «እምብዛም ሞኝነት ለበግም አልበጃት፣ አስራ ሁለት ሆና አንድ ነብር ፈጃት» ነው አይደል የሚባለው። አስትያይቱም ሆነ ጥያቄው በእውነት ለአንዲት ኢትዮጵያ ከማሰብ የፈለቀ መሆኑን ብረዳም። ሌላው አማራውን ለማጥፋት ተደራጅቶ በመስራት ላይ እያለ። አማራውን ግን ተደራጅተህ እራስህን አትከላከል ማለት ፍትሃዊ አይመስለኝም።
ይልቁንም የቅን መንፈስ ባለቤ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን መሰንዘር የነበረበት አስተያይት። አማራው ሲደራጅ ኢትዮጵያዊ እነቱን ማዕከል ማድረግና ጠላቱን በደረጃ ለይቶ በማስቀመጥ። ጸረ ህዋሃት አቋም ካላቸው አካላት ጋር ሁሉ ሳይናቆር ተባብሮ መስራት አለበት። የሚለው ቢሆን ኖሮ ለእኔ ተመራጭና ተደማጭም ይሆናል የሚል እምነት አለኝ።
ያምሆነ ይህ ትግሉ የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅድ ተነድፎለት በሳምንታት ወይንም በወራትና በአመት ተወስኖ የሚያልቅ። ወይንም እንደብርጭቆ ውሃ በአንድ ቃታ የሚጨለጥ ባለመሆኑ ቀንን ቀን ሲተካው እያየን ነው።
እንዲህ የድሉ ጊዜ በራቀ ቁጥር ደግሞ በአማራው ነግድ ላይ በግልጽ የታወጀው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ከመቸውም ጊዜ በላይ በረቀቀ ስልት ተጠናክሮ ቀጥሏል። በአኳያው«ባለቤቱ ካልጮኽ፣ ጎረቤት አይረዳም» እንዲሉ ነውና። አማራው እራሱ ተደራጅቶ እየደረሰበት ያለውን በደል ዝቅ ሲል የኢትዮጵያ ከፍሲል የዓለም ህብረተሰብ እንዲያውቀው የማድረግ ስራ መስራት አለበት የሚል እምነት አለኝ።
ለዚህም በአማራው ላይ የደረስውንና እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ እየተከታተለ መረጃዎችንና ማስርጃዎችን በማሰባሰብ ለሚመለከተው ማቅረብ የሚችል አካል የግድ ያስፈልጋል ማለት ነው።
ይህንን ሃላፊነት እንደተባለው የህብረ ብሄር ድርጅቶች መውሰድ አለባቸው እንዳንል። የሚያስኬድ አይሆንም።
ምክናያቱም ህብረብሄር ድርጅቶች የሚያተኮሩት በአጠቃላዩ ወያኔን በማስወገዱ ትግል ላይ እንጅ አንዱን ብሄር ብቻ ነጥለው አማራው ግፍ ተሰርቶበታል፣ ያለሃጢያቱ ተወንጅሏል፣ አማራው ጨቋኝ አልነበረም፣ አይደለም። በማለት ለህዝብ ለማስረዳት። የተለየ መርሃግብር ነድፈው ስለ አማራው ብቻ ሊሰሩ ስለማይችሉ።
በዚህ ከተስማማን «የአገሩን በሬ፣ በአገሩ ገበሬ» ነውና። ይህንን ሃላፊነት በመውሰድ አማራው እራሱ ተደራጅቶ ህብረብሄር ድርጅቶች ሊሰሯቸው የማይችሏቸውንና በቀጥታም ለነጻነት ትግሉ ከፍተኛ ድርሻ ሊኖራቸው የሚችሉትን ከዚህ የሚከተሉትን ስራዎች መስራት አለበት ብየ አስባለሁ።
እነሱም
1.አማራው ባለፉት መንግስታት ሁሉ እንደማነኛውም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰብ። ሲበደል የኖረ እንጅ ጨቋኝና በዝባዥ እንዳልነበር። ለዓለምም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሁም ለእራሱ ለአማራው ወጣት ትውልድ በማስርጃ አስደግፎ በማቅረብ እንዲያውቀው ማድረግ።
2.አማራው ነፍጥኛ፣ ትምከተኛ፣ ቢሮክራት ነህ። እየተባለ በማንነቱ እንዲያፍርና አንገቱን እንዲደፋ የተደርገው። በጠላቱ የተለጠፈበት በውሽት የተቃኘ የስም ማጥፋት ታሪክ መሆኑን በተጨባጭ በማስርዳት አንገቱን ቀና አድርጎ ለመብቱና ለነጻነቱ እንዲታገል መቀስቀስ።
3. አማራው ፈሪነህ በሚል የተከፈተበትን የስነልቦና ጦርነት ለማክሽፍ ትግስተኛና አርቆ አሳቢ እንጅ ፈሪ እንዳልሆነ በማስርዳት አጻፋዊ የስነ ልቦና ጦርነትን ማፋፋም።
4.የዘር ማጽዳት አዋጅ የታወጀበት በእሱ ስለሆነ። የወያኔ ከስልጣን መወገድ ከማነኛውም ኢትዮጵያዊ የበለጠ የሚጠቅመው ለአማራው መሆኑን በተጨባጭ በማስረዳት ለነጻነት ፍልሚያው ግንባር ቀደም ተዋናይ እንዲሆን ማንሳሳት።
5.ከንጉሱ ወደ ደርጉ፣ ከደጉ ወደ ወያኔ፣ በተደረግው የመንግስት ሽግግር ወቅቅት በአማራው ላይ የተፈጸመውንና አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለውን መለኪያ መስፈርት መግለጫ ቃላት የማይገኝለትን ግፍ በማስርዳት ከ3ኛ ዙር ጥቃት እራሱን እንዲከላከል ማዘጋጀት።
6.በአሳለፍነው ግማሽ ምዕተ አመት በአማራው ላይ የተፈጸሙ ዝግናኝ ድርጊቶች ከሚፈጥሩት የበቀል አስተሳሰብ በመውጣት ስለወደፊቱ እንዲያስብ ማድረግ።
7.ወደፊት የአማራው ወጣት ትውልድ ጽንፈኛ እንዳይሆን። ከእራሱ ከአማራው ድርጅት። አማራነትና ኢትዮጵያዊነት አንዱ ያለአንዱ የማይቆሙ ደምና ስጋ እንደሆኑ ያውቅ ዘንድ ማስተማር።
የሚሉት ከብዙ በጥቂቱ ህብረብሄር ድርጅቶች ከማይሰሯቸው ስራዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው ብየ አስባለሁ።
አዎ!! በእኔ እምነት ከድብቅ የግል ፍላጎት በጸዳና ቅንነትን በተላበሰ ስብና ላይ ሆኖ ለሚያየው ሰው። አማራው እራሱን አደራጀና አጠናከረ ማለት። ለትግሉ ታላቅ አስተዋጾ አደረገ ማለት ነው እንጅ። ለህብረብሄር ድርጅቶች እንቅስቃሴም ሆነ ለኢትዮጵያ አንድነት ስጋት ወይንም እንቅፋት አይሆንም።
ነገሩ እንደዚህ ሆኖ እያለ በአለፉት 26 አመታት ውስጥ ከአማራው በቀር በኢትዮጵያ አለየሚባለው ብሄረሰብ ወይንም ነገድ። በማንነቱ ሲሰባሰብና እንዲያውም አብዛኛው ማለት በሚያስችል ሁኔታ። አማራውን ጠላቴ ብሎ ሲደራጅ።የከለከለ አይደለም የተናገር እንኳን አልነበረም።
ዛሪ የአማራው ህዝብ አማራ በመሆኑ ብቻ በሁሉም ወገኑ እስከመጨረሻው ጠርዝ መገፋቱ፣ መገለሉና በገደሉ፣ መፈናቀሉ ሲበዛበት። ይህ ሁሉ በደል የደረሰብኝ በአማራነቴ ስለሆነ በማንነቴ ተደራጅቸ እራሴን ከሁለንተናዊ ጥቃት እከላከላለሁ። ዘሬን ጨርሶ ከመጥፋት እታደጋለሁ ማለት ሲጀምር ለምንድን ነው የብዙው ሰው አይን ደም የለበሰው? ዘሩ ከምድረግጽ እስኪጠፋ እንዲጠብቅ ነው ወይ የሚመከረው የሚለው ጥያቄ ለእኔ እስካሁን መልስ ያላገኘሁለት ነው።
ኢትዮጵያዊ የአማራ ተጋድሎ ያሽንፋል!!!
ማተቤ መለሰ ተሰማ
ኢሜል matebemelese@yahoo.com
ጥር ወር 2009 ዓ.ም

ትንሳኤ አማራ ማናት

ትንሳኤ አማራ የአማራን ህዝብ ሁለንተናዊ ህልውን አድጋ ላይ የጣልውን የህወሀትን አስተዳደር ለመጣልና በመትኩ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት እንዲሁም የአማራ ህዝብ በቀደመ ክብሩና ሙሉ የሀገር ባለቤትነቱን አስከብሮ ፍጹም ፍትሀዊነት በሰፈነበት ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ምህዳር ውስጥ ከእህት ማህበረሰቦች ጋር በቀደመው ፍቅርና ሰላም እንዲኖር የበኩላችንንን ጥረት ለማድረግና ሀሳባችንን፡ እምነቴንንና እይታችን ለወገኔ ለማካፈል እንችል ዘንድ ከ2006 ዓም ጀምሮ ለዚሁ አላማ ስንንቀሳቀስ በነበርን የአማራ  ልጆች የተከፈተች ገጽ ናት።

የትንሳኤ አማራ ራዕይ፡ 

ራዕያችን የዐማራ ሕዝብ ከሚደርስበት ማንነቱን መሰረት ያደረገ የተቀናጀ ጥቃት ነጻ ወጥቶ፤ በመላው ኢትዮጵያ በነጻነት ተንቀሳቅሶ የመኖርና ሀብት ንብረት የማፍራት መብቱ ተከብሮ፣ የማንነት ክብሩና ልዕልናው ተረጋግጦ፣ ሙሉ የዜግነትና የሀገር ባለቤትነት መብቱን ተከብሮ ማየት፤ እንዲሁም የሕግ የበላይነት በተረጋገጠባት፣ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞከራሲያዊ መብቶች በተከበረባት፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ከሕዝብ የሚመነጭና ለሕዝብ ፍላጎት የሚገዛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሰፈነባት፥ ለሁለንተናዊ ልማት ተባብሮ በሚሰራ ማህበረሰብ በተገነባች፣ አንድነቷና ዳር ድንበሯ በተጠበቀ በስልጣኔ የቀደመች ኢትዮጵያ ውስጥ የአማራ ህዝብ ማህበራዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና፣ ፖለቲካዊ ጥቅሞቹ ሳይሸራረፍ ተከብሮ ማየት ነው።

 የትንሳኤ አማራ ተልእኮ፡

  1. ማንቃት፡-

የትንሳኤ አማራ የመጀመሪያ ተልእኮ አማራው ህዝብ ታሪካዊ ማንነቱን የሚያውቅ፣ ወቅታዊ ፖለቲካዊ፡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶቹን በአግባቡ የሚለይ፤ ጠላት በረቀቀ መንገድ የሚያደርስበትንና ያደረሰበትን ጥቃት መመርመርና መረዳት እንዲችል ማስቻል፡ የአማራ ወንድማማችነትን አስፈላጊነትና ሊከወኑ የሚገባቸውን ተግባራት ማስተዋወቅ፡ ከእህት ብሔረሰቦች ጋር ሊኖረው ስለሚገባ ገንቢ መስተጋብር እንዲሁም ጠላቶቹን ለይቶ ለማየት ስለሚያስችሉ ጉዳዮች በበቂ መረጃ ላይ የተመሰረተ የህዝብ ግንኙነት ስራ በመስራት ማስተዋወቅ ነው፡፡

  1. ማብቃት፡-

 የአማራ ህዝብ በመላው ኢትዮጵያ በያለበት አካባቢ በፖለቲካዊ፡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅሙ የጎለበተ መሆን እንዲችል፤ ብሎም የህዝባዊ ስልጣን ባለቤትነቱን ለማረጋገጥ እንዲችል፤ ማህበራዊ፡ ታሪካዊ፡ ፖለቲካዊና ባህላዊ እውቀቱና አመለካከቱና ስነልቦናው ዳብሮ በኢኮኖሚያዊ ውድድሮች ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችለው አቅም ፈጥሮ፤ እራሱን ከማንኛውም ጥቃት ሊከላከልበት የሚያስችል ትሥሥርና አደረጃጀት ፈጥሮ፤ ከሌሎች ዜጎች ጋር በእኩልነት መርህ የሚኖርባት ሀገር ባለቤት መሆን እንዲችል የበኩላችንን አስተዋጾ ማድረግ ሁለተኛው አብይ ተልእኮአቸን ነው።